
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን ሲያከናውኑ የነበረው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው በተለምዶ ፋንታ ሰፈር እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ማሩን ለማዘጋጀት የሚጠቀሙባቸውን በረዶ መሰል ኬሚካል፣ቀይ እና ነጭ ዱቄት መሰል ፓውደር፣ እንጉዳይ መሰል እና 5 ኩንታል ሰኳር በአምሰት በርሜል ሲዘጋጅ የነበረ ማር እና ተዘጋጅቶ ለገበያ ሊውል የነበረ ዘጠኝ ማዳበሪያ ማር መሰል ተይዟል።