መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 24፣2012-አጫጭር መረጃዎች

~ በኬንያ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች የመከላከያ አልባሳትን በድጋሚ እንዲለብሱት እየተገደዱ ይገኛል፡፡በቁሳቁስ እጥረት ተጋላጭ ስለመሆናቸዉ የጤና ባለሙያዎቹ መናገራቸዉን ዴህሊ ኔሽን ዘግቧል፡፡

~ በህንድ የሚገኙት ፖለቲከኛ የአልኮል መጠጥ ቤቶች ይከፈቱ ማለታቸዉ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡የተቃዋሚዉ ኮንግረስ ፓርቲ አባል የሆኑት ሲንጋህ አልኮል እጆቻችንን እንደሚያጸዳዉ ሁሉ ዉስጣችንም በአልኮል መጽዳት አለበት ብለዋል፡፡አልኮል መጠጣት ለኮሮና ወሰኝ ነዉ ሲሉ ቢናገሩም የአለም የጤና ድርጅት ግን እንደማይጠቅም መናገሩ ይታወሳል፡፡

~ በፈረንሳይ እንቅስቃሴ የሚገድበዉ ህግ ከ10 ቀናት በኃላ የሚነሳ ቢሆንም ህይወት ወደነበረበት ግን በዚህ ቀናት ዉስጥ አይመለስም ሲሉ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስጠነቀቁ፡፡

~ ሩዋንዳ ከሰኞ ጀምሮ እንቅስቃሴን የሚከለክለዉ ህግ ላይ ማሻሻያ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡ማልታ በተመሳሳይ ክልከላዎችን ቀስ በቀስ እንደምታነሳ አስታዉቃለች፡፡

~ ጀርመን በቀጥታ ስርጭት ለአራት ቀናት የሚካሄደዉን የሜዳ ቴኒስ ዉድድር በዛሬዉ እለት አስጀመረች፡፡ዉድድሩ ያለ ደጋፊዎች እይታ ይካሄዳል፡፡

~ በሚሊየን የሚቆጠሩ የአለም ህጻናት በወቅቱ ማግኘት የነበረባቸዉን ክትባት ማግኘት አለመቻላቸዉ ተነገረ፡፡በኮሮና ቀዉስ የተነሳ በተፈጠረ የመጓጓዣ ችግር ስለመሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታዉቋል፡፡

~ በዌልስ ለሚገኙ የማህበራዊ ክብካቤ ባለሙያዎች ለእያንዳንዳቸዉ የ500 ፓዉንድ ድጋፍ ሊደረግ ነዉ፡፡ከ64ሺ በላይ ሰራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ለዚህም 32.2 ሚሊየን ፓዉንድ ተመድቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *