መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 24፣2012-አጫጭር መረጃዎች

~ የአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ለኢቦላ የሚሰጠዉን ረምድሲቪር የተባለ መድሃኒት ለኮሮና ህሙማን እንዲሰጥ ዉሳኔ አሳለፈ፡፡በቅርቡ የተደረጉ የምርምር ዉጤቶች እንዳሳዩት ከሆነ ህሙማን በቶሎ እንዲያገግሙ እገዛ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

~ በስፔን ከሰባት ሳምንታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአዋቂዎች ከቤት መዉጣት ተፈቀደ፡፡በተመሳሳይ ኦስትሪያ ሱቆች፣የዉበት ሳሎኖች በድጋሚ እንዲከፈት ዉሳኔ አሳልፋለች፡፡

~ በየመን ታኢዝ ግዛት የኮረና ቫይረስ የተያዘበት ሰዉ መገኘቱ ተሰማ፡፡በአሳ ገበያ ዉስጥ የነበረ ሰዉ በቫይረሱ መያዙ ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ንኪኪ የነበራቸዉ 10 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ተወስደዋል፡፡

~ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(IMF)ለኢኳዶር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ በሚል የ643 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብድር ማጽደቁ ተሰማ፡፡በኢኳዶር 4,675 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸዉ ሲረጋገጥ የ883 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ በሲንጋፖርት ከሁለት ሳምንት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዝቅተኛ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ባለፉት 24 ሰዓት ተመዘገበ፡፡447 ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓት በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 17,548 ሲደርስ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ አፍጋኒስታን የኮሮና ቫይረስ የከፋ ጥፋት ሊያደርስባት እንደሚችል በአሜሪካ የተሰራዉ ጥናት አመላክቷል፡፡በሀገሪቱ የቀጠለዉ ግጭት ለስርጭቱ መስፋፋት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡

~ በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ዉስጥ በምትገኘዉ ሊባኖስ 75 በመቶ የሀገሪቱ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ እና በሀገሪቱ ባለዉ የኢኮኖሚ መዳከም የተነሳ ድጋፍ እንደሚያሻቸዉ የሊባኖስ የማህበራዊ ጉዳዮች ሚንስትር ራሚዝ ሙሻራፊ ተናገሩ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *