መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 26፣2012-በኖቭል ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ ቻይና መመለስ ያለባት ጥያቄዎች አሉ ሲሉ የእንግሊዝ የመከላከያ ዋና ፀሀፊ ቤን ዋላስ ተናገሩ፡፡

ዋላስ ከ LBC ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ ቻይና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ረገድ ተጠያቂ ናት ወይ? ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹ሲመስለኝ አዎን ይኖርባታል፡፡ ቻይና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቫይረሱ ምን እንደተማረችና ወደ ስኬት እንደመጣች በግልፅ መናገር ይጠበቅባታል›› ብለዋል፡፡

ቤን ዋላስ በወርሃ መጋቢት መባቻ ላይ በቫይረሱ ተጠቅቶ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ከቫይረሱ አገግሞ ወደ ስራ መመለሱ ነው የተነገረው፡፡

ከስካይ ጋር በነበረው ቆይታ በቫይረሱ መያዝ ያለውን ስሜት ተጠይቆ ሲመልስም ‹‹ ፍላጎትና ሀይሌን ፣ በጊዜያዊነትም የማሽተትና የማጣጣም ስሜቶቼን አሳጥቶኝ ነበር›› ብለዋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ ማይክ ፖምፒዮ በበኩላቸው ‹‹የኮሮና ቫይረስ መነሻ የቻይና ላብራሪ ስለመሆኑ ማስረጃ እንዳላቸው ገልፀዋል›› ነገር ግን ሰው ሰራሽ ነው ወይ በሚለው ዙሪያ የአሜሪካ የክትትል ኤጀንሲዎች ማረጋገጫ አልሰጡም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *