
ስደተኞቹ የተያዙት ባሳለፍነው አርብ ከምዕራቧ ከሄራት አውራጃ በህገወጥ መልኩ ኢራን ሊገቡ ሲሉ ነበር።
በኢራን የድንበር ጠባቂዎች እጅ ከወደቁ በኋላም ድብደባና እንግልት ብሎም ወደ ባህር መወርወራቸው ነው የተሰማው። አንዳንዶቹ ህይወታቸው ስለማለፏ ቢነገርም ኢራን ግን ውንጀላውን አስተባብላለች።
በሁለቱ ሀገራት ድንበር መካከል ሀሪሩድ ከተሰኘው ባህር ነበር የተወረወሩት።
ድርጊቱ ተፈፀመ የተባለው በአፍጋን ግዛት ነው በኢራን ሳይሆን እናም የደህንነት ጠባቂዎቹ እጃቸው የለበትም ሲል የኢራን ውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ ገልጿል።
የስደተኞቹ ቁጥር ያልተገለፀ ሲሆን ባለስልጣናት ግን በርካታ ስለመሆኑና ቢያንስ የሰባት ሰዎች ህይወት ስለማለፏ ጠቁመዋል። በባህሩ ዙሪያ ፍለጋውም ቀጠለ።