መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 27፣2012-በአውሮፕላን መከስከስ በሶማሊያ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

የሶማሊያ ትራስፖርት ሚኒስትር እንዳስታወቀዉ ለኮሮና ቫይረስ ህክምና ድጋፍ የሚውሉ ቁሳቁሶችን ጭኖ ሲያጓጉዝ የነበረው አውሮፕላን ተከስክሶ አብራሪውን ጨምሮ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በአደጋዉ ህይወታቸዉን ካጡት መካከል ዋና እና ረዳት አብራሪ፣የበረራ ቴክኒሺያን፣ሰልጣኝ አብራሪ እና ሌሎች ሁለት የበረራ ክፍል አባላት ይገኙበታል፡፡ከሟቾቹ መካከል የአምስቱ አስክሬን የተገኘ ሲሆን የአንዱ በፍለጋ ላይ እንደሚገኝ የሶማሊያ የትራንስፖርት ሚንስትሩ ሞሃመድ ሳላድ ተናግረዋል፡፡

የአዉሮፕላን መከስከስ ያጋጠመበት የደቡባዊ ሶማሊያ ቤይ አዉራጃ ባርዳሌ ከተማ አቅራቢያ ሲሆን ስፍራዉ የአልሻባብ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱበት ስለመሆኑ በሮይተርስ ዘገባ ላይ ተመልክቷል፡፡

የሶማሊያ የዜና ኤጀንሲ አዉሮፕላኑ ንብረትነቱ የአፍሪካ ኤክስፕረስ አየር መንገድ መሆኑን አስታዉቋል፡፡ከሞቃዲሾ ባይደዋ ከዛም ወደ ባርዳሌ እያመራ መከስከሱን ያሳወቀዉ አየር መንገዱ የአደጋዉ ሁኔታ ግልጽ አለመሆኑን አስታዉቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *