መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 27፣2012-ቬንዙዌላ ባሳለፍነዉ እሁድ ተሞክሮ ከከሸፈዉ የሴራ አመጽ ጋር በተያያዘ ሁለት የአሜሪካ ዜጎች እጃቸዉ አለበት ስትል በቁጥጥር ስር አዋለቻቸዉ

እሁድ እለት ከሽፏል በተባለዉ የግጭት ጥንስስ ስምንት ሰዎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉ ይታወሳል፡፡የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እንዳስታወቁት ከሆነ ከዚህ ሴራ ጀርባ የዋሽንግተን መንግስት እጅ አለበት ብለዋል፡፡13 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ስለመዋላቸዉ ገልጸዋል፡፡

ማዱር በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ሁለቱ አሜሪካዉያን አሪያን ቤሪ እና ሉክ ደንማን እንደሚባሉ በመግለጽ በአሜሪካ ጦር ዉሰጥ ተሳትፎ ያላቸዉ ሰዎች መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡ስለ ግለሰቦቹ ማዱሮ ሲገልጹ እንደ ራምቦ ደግሞም እንደ ጀግና ሲጫወቱ ነበረ ሲሉ አስገራሚ አስተያየ ሰንዝረዋል፡፡

አሜሪካ በኒኮላስ ማዱሮ አስተዳደር ላይ ተደጋጋሚ የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣሏ ይታወቃል፡፡አሜሪካ በዚህ ጉዳይ እጇ እንደሌለበት ግን አስታዉቃለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *