
35 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ከወሎ ሰፈር ኡራኤል እየተገነባ ያለው መንገድ 1ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በአንድ ጊዜ 6 የተሽከርካሪዎችን ማጓጓዝ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ከመንገድ ግንባታው ጋር በተያያዘ ሲነሱ የነበሩ የወሰን ማስከበር ችግሮች መፍትሄ ማግኘታቸው ና ግንባታው ከግማሽ በላይ መጠናቀቁም ነው የተገለጸው።
በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ መንገድ የብስክሌት መንገድንም ያካተተ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።