መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 28፣2012-በአፋር ክልል በሚገኙ የለይቶ ማቆያ ቦታዎች ላይ ጉብኝት ተደርጓል

የሰላም ፣ የጤና ፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እንዲሁም የሰላም ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የሆኑት የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን፣የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የተዉጣጡ ከፍተኛ የስራ አመራሮች በአፋር ክልል የለይቶ ማቆያ ቦታዎች በመገኘት የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባዉና የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሃርላ አብዱላሂ ፤ በሰመራ ዩኒቨርስቲ ተገኝተዉ የኮረና ቫይረስን ስርጭት ከመከላከል አኳያ ምን ምን ስራዎች እየተከናወኑ እንዳለ ስራዉን እያከናወኑ ያሉ ኮሚቴዎችን አነጋግረዋል።

በድንበር በኩል የሚገቡ ከስደት ተመላሽ ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችንና የፀጥታ አካላትን አበረታተዋል።

የኮቪድ19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመከላከል መንግስት የተለያዩ እርሞጃዎችን እየወሰደ የሚገኝ ሲሆን ከተለያዩ ሀገራት አቋርጠዉ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ዜጎችን በድንበር አካባቢ የማቆያ ቦታዎችን በማዘጋጀት ወረርሽኙን እየተከላከለ ይገኛል።

በቀጣይ በሌሎች የድንበር አካባቢዎች በመገኘት ወርርሽኙን ለመከላከል እየተደረገ ያለዉን ጥረት የአሰራር ቅኝት ይደረጋል መባሉን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *