መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 28፣2012-የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሰሜን ኮርያን መሪ ኪም የክብር ሜዳል መሸለማቸዉ ተሰማ

በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት የሶቬየት ወታደሮች በሰሜን ኮርያ ህይወታቸዉን ያጡ ሲሆን ለነዚህ ወታደሮች ሰሜን ኮርያ መታሰቢያ እንዲኖራቸዉ አድርጋለች በሚል ሩሲያ እዉቅናን ሰጥታለች፡፡በፒዮንግ ያንግ የሩሲያ ኤምባሲ ሽልማቱን በትላንትናዉ እለት ለሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ አን እንዲደርስ አድርገዋል፡፡

ለሰሜን ኮርያ መሪ የተበረከተዉ ሜዳል ላይ የታላቁ የአርበኝነት ጦርነት 75ኛ ዓመት ድል የሚል ጹሁፍ ሰፍሮበታል፡፡ኪም በሀገሪቱ የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በኩል ሽልማታቸዉን ተቀብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *