መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 28፣2012-የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን 7,723 ካሬ ሜትር ስፉት ያለውን የስፖርት ማዝወተሪያ ስታዲየም ግንባታ ለማስጀመር የመስክ ምልከታ ተደረገ

በመስክ ምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይን ጨምሮ የንፋስ ስልክ ክ/ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ፣ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የቦርድ አመራሮች እና ስራ አስኪያጆች በስፍራው ተገኝተዋል።

ከማልማት ጋር ተያይዞ ለማስጀመር ያሉ ችግሮችን በዝርዝር በመለየትና በመገምገም ከአመራሮቹ ጋር መግባባት ላይ በመደረሱ ወደ ልማት እንደሚገባ ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *