መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 28፣2012-የ43ኛው ኢትዮጲያዊው ሰው ህይወት አልፏል

ከዘጠኝ አመታት በፊት 43 የኩላሊት ህሙማን ችግራቸዉን ለማሰማት በመንግስት ዘንድ ስለ ኩላሊት ህመም እዉቅና እንዲሰጠዉ ለማስቻል የኩላሊት እጥበት የበጎ አድራጎት ድርጅትን ይመሰርታሉ፡፡ታዲያ ከጤና መቃወስ ባለፈ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራን የሚያስከትለዉ የኩላሊት መድከም ችግር የ42ቱን መስራች አባላት ህይወት ለመቀማት ስድስት አመት ብቻ ወስዷል፡፡ማህበሩን መስርተዉ ከነበሩ 43 አባላት መካከል በህይወት የነበሩት አቶ የሱፍ አብዱልሃሚድ በትላንትናዉ እለት ህይወታቸዉ ማለፉን የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለብስራት ሬድዮ አስታዉቀዋል፡፡

በዘውዲቱ መታሰቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ድርጅቱ ለዲያለሲስ ምቹ አድርጎ ያሰራውን የዲያሊሲስ ማዕከል ሲገነባ በግላቸው የሚያውቋቸውን ግለሰቦች በማስተባበር ማዕከሉን ያስገነቡ ሲሆን ድርጅቱ ከውጪ አገር ሃኪሞች ጋር ግንኙነት እንዲኖረው በሰሩአቸው ሥራ ምክንያት አሜሪካ ከሚገኘው ሲአትል አውት ሪች ከተባለ ድርጅት ጋር በመፃፃፍ በሚሊዮን የሚቆጥር ግምት ያላቸው የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች በልገሳ ለድርጅቱ እንዲመጣ አስደርገዋል፡፡

አቶ ዮሱፍ አብዱለሃሚድ ሃኪሞች ያለማቋረጥ ከውጪ በየዓመቱ ወደ ሃገራችን እንዲመጡ በማስደረግ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን የኤቪ ፊስቱላ መለስተኛ ጥገና ህሙማኑ በነፃ እንዲያገኙ አስችለዋል፡፡ አቶ ዮሱፍ አብዱለሃሚድ በሣምንት ሦስት ግዜ በኮሪያ ሆስፒታል የዲያሊሲስ ህክምና እያገኙ የነበር ሲሆን በትናንትናዉ እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡

አቶ ዮሱፍ አንዱላሃሚድ የአምስት ልጆች አባት እና ባለትዳር የነበሩ ሲሆን ህይወታቸው አስካለፈበት ሰዓት ድረስ ለኩላሊት ህሙማኑ ያለምንም መሰልቸት በቅንነት ሲያገለግሉ ቆይተው በተወለዱ በ73ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *