መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 29፣2012-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉ 5 ተከሳሾች በቀላል እስራትና በገንዘብ መቀጮ ተቀጡ

በአንድ ጠባብ ቤት ውስጥ አምስት በመሆን ተሰብስበው ጫት በመቃም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅንና አዋጁን ለማስፈፀም የወጣውን ደንብ የተላለፉ አምስት ተከሳሾች በ 3 ወር ቀላል እስራትና በ 3000 ብር የገንዘብ መቀጮ ተቀጡ፡፡

በእነ መሰፍን ጠና ስም በሚጠራው መዝገብ በአምስት ተከሳሾች ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ጽ/ቤት ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን ተከሳሾች የአዋጁን አንቀፅ 6 እና አዋጁን ለማስፈፀም የወጣውን ደንብ አንቀፅ 3 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በአንድ ጠባብ ቤት ውስጥ አምስት በመሆን ተሰብስበው ጫት የቃሙና አራትና ከአራት በላይ ሆነው በመሰብሰባቸው የተነሳ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሾ የሆነው ተከሳሾችን ሰብስቦ ጫት በማስቃሙ የሶስት ወር ቀላል የእስራት ቅጣት እንዲቀጣ የተፈረደበት ሲሆን ቀሪዎች አራት ተከሳሾች ላይ ከአራት በላይ ሆነው ተሰብስበው የተገኙ በመሆኑ በ 3000 (ሶስት ሺ ብር) የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል፡፡

በሌላ በኩል አቃቂ ቃሊቲ በክፍለ ከተማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉ ከ 120 በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው የሚገኝ ሲሆን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎትም ከ 78 በላይ በሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ላይ የተለያየ ይዘት ያለው ውሳኔ የወሰነ ሲሆን በ52 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ምንጭ:- የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *