መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 30፣2012-በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ።

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያው መነሻውን ከምራብ ጎንደር ዞን ምድረ ገነት ከተማ አስተዳደር ወደ ጎንደር ከተማ ባደረገ የጭነት ተሽከርካሪ አይሱዙ ሻግ (እቃ መደበቂያ) ውስጥ ተደብቆ ወደ ጎንደር ለማለፍ ሲሞክር ነው የተያዘው።

በተደረገ ፍተሻ 37 ክላሽ፣ 9 ሺህ 277 የክላሽ ጥይቶች እንዲሁም 21 የክላሽ ካዝናዎች በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በልዩ ኃይል አባላትና የመደበኛ ፖሊስ አባላት ትብብር መያዙን ከአርማጭሆ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *