መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 1፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በስሎቫኒያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሳይክል አደባባይ በመዉጣት መንግስት በኮሮና ቫይረስ የተነሳ እንቅስቃሴ መከልከሉን አዉግዘዋል፡፡ሰልፈኞቹ ባለስልጣናት ከማስክ እና ቬንትሌተር ግዢ ጋር በተያያዘ ሙስና ተፈጽሟል የሚል ሪፖርት መዉጣቱን ተከትሎ መንግስትን አብጠልጥለዋል፡፡

~ በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙርያ የሰሜን ኮርያ መንግስት ድጋፍ ካስፈለዉ ቻይና እኔ አለዉ አለች፡፡የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ አን ቻይና ኮሮናን በመከላከል ላስመዘገበችዉ ድል እንኳን ደስ አለሽ ሲሉ ለቻይና ፕሬዝዳንት ሺ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

~ ኢራን 40 ሺ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያን ጀርመንና ቱርክን ጨምሮ ለበርካታ ሀገራት ስለመላኳ የሀገሪቱ የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጃቫድ ዛሪፍ ተናገሩ፡፡

~ የፓራጓይ ፕሬዝዳንት ማሪዮ ቤኒቴዝ ኮሮና በጎረቤት ሀገር ብራዚል ካደረሰዉ ጥፋት አንጻር ሀገራቸዉ ቫይረሱን ለመቆጣጠር የወሰደችዉ እርምጃ ስኬታማ ነዉ ሲሉ ተናገሩ፡፡

~ በአፍጋኒስታን በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረዉን ጫና ለመቀነስ መንግስት ለድሆች ምግብን እያከፋፈለ የሚገኝ ሲሆን ክፍፍሉ ፍትሃዊነት ይጎድለዋል በሚል በተነሳ ተቃዉሞ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

~ ከሶስት ወራት በኃላ በቻይና መዲና የሚገኙ የስፖርት ማዝወተሪያዎች (Gyms) በድጋሚ እየተከፈቱ ሲሆን ማስክ የማድረግ ግዴታ ደንበኞች አለባቸዉ፡፡

~ በፊሊፒንስ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር 704 ሲደርስ የተጠቂዎች ቁጥር ከ10ሺ በላይ ሆኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *