መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 3፣2012-በኦሮሚያ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ የሌሊት ጉዞ ያደረጉ አሽከርካሪዎች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ተቀጡ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ አዋጅ በመጣስ በአጠቃላይ 581 ተሸከርካሪዎች ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡

ከነዚህም ውስጥ 352 የሚሆኑ ተሸከርካሪዎች የሌሊት ጉዞ በማድረጋቸው ከ2 ሚሊየን ብር በላይ እንደተቀጡ ተገልጿል።

በተጨማሪም ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በማድረግ 45 የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች ላይ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን ፤ ዘጠኙ ንግድ ፍቃዳቸው ተቀምቶ እንዲዘጋ ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ደራ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ አይሱዙ ተሸከርካሪ 640 ብዛት ያለው ባለ 20 ሊትር ዘይት ይዞ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር በማዋል ፤ ህገ ወጥ ዘይቱ ለክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገቢ ተደርጓል፡፡

እንዲሁም በእህል ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ እና የሸሸጉ 3 የእህል መጋዘኖች ላይ እርምጃ መወሰዱን በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮምኒኬሽን ዲቨዝን ሀላፊ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ወርቁ ለብስራት ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *