መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 3፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች


~ በቼክ ሪፐብሊክ ከኮረና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የወጡት መመሪያዎች መላላት ጀምረዋል፡፡ትምህርት ቤቶች፣የዉበት ሳሎን፣ሲኒማ በድጋሚ መከፈት ጀምረዋል፡፡የአልኮል ሽያጭ የተፈቀደ ሲሆን ከ100 በላይ ሆኖ መሰብሰብ ግን ተከልክሏል፡፡በቼክ 280 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡
~ ዛምቢያ ከታንዛኒያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች፡፡ናኮንዲ በተባለ ድንበራማ ስፍራ ላይ በ85 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ በ24 ሰዓት ዉስጥ መገኘቱን የዛምቢያ የጤና ሚንስቴር አስታዉቋል፡፡
~ በስድስት የገልፍ አረብ ሀገራት በኮረና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100ሺ በላይ ሆነ፡፡ሀገራቱ ሳዑዲ፣ኳታር፣ኦማን፣ኢምሬትስ፣ባህሬን ችና ኩዌት ናቸዉ፡፡ከተጠቂዎቹ ባለፈ በስድስቱ ሀገራት የ557 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
~ ኒዉዝላንድ ካፌዎች፣ሲኒማ ቤት እና የስፖርት ማዝወተሪያ ከሀሙስ ጀምሮ ክፍት እንደሚደረግ አስታወቀች፡፡1‚147 ሰዎች በሀገሪቱ በቫይረሱ ሲጠቁ 93 በመቶ አገግመዉ ከሆስፒታል ወጥተዋል፡፡
~ የሴኔጋል ቅዱስ ከተማ በምትባለዉ ቱዩባ በድጋሚ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መዛመት ስጋትን ወልዷል፡፡ቱዩባ ሁለተኛዋ መካ በመባል ትታወቃለች፡፡
~ ኬንያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚል 7000 ታራሚዎችን ከእስር መልቀቋ ተሰማ፡፡
~ የእንግሊዝ መንግስት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልባለ ሀምሳ ገፅ ሪፖርት በዛሬው እለት ይፋ ያደረገ ሲሆን ት/ቤቶች ቀስ በቀስ ከሰኔ አንድ ጀምሮ ክፍት እንደሚደረጉ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *