መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 4፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ የአለማችን ግዙፉ እና በዱባይ የሚገኘዉ ቡርጃ ከሊፋ ህንጻ ለተጎጂዎች ገንዘብ ማሰባሰቢያ አላማ እየዋለ ይገኛል፡፡የህንጻዉ የዉጪ ገጽታ 1.2 ሚሊየን አንፖሎች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱን አንፖል በ10 ድረሃም በመግዛት ለረድኤት ተግባር ይዉላል፡፡10 ድርሃም ለአንድ ምግብ ግዢ በቂ ሲሆን በኢምሬትስ በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ ለተቸገሩ የሚለገስ ይሆናል፡፡

~ የአለም አቀፉ የነርሶች ቀን በዛሬዉ እለት ሲከበር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ነርሶች እያደረጉት ስለሚገኘዉ ጥረት ፖፕ ፍራንሲስ አመስግነዋል፡፡

~ በኮሮና ቫይረስ ቀዉስ የተነሳ የለንደን የህዝብ ትራንስፖርት ኔትወርክ አገልግሎት የ4.9 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ኪሳራ በተያዘዉ ዓመት ያጋጥመዋል ተባለ፡፡በመላዉ ዩናይትድ ኪንግደም በቫይረሱ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር 32,065 ደርሷል፡፡

~ ሴኔጋል ከዛሬ ጀምሮ የእምነት ተቋማትና የገበያ ማዕከላት ክፍት አድርጋለች፡፡በሴኔጋል 19 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

~ የኮሮና ቫይረስ መነሻ እንደሆነች በምትታመነዉ የቻይና ዉሃን ከተማ ለነዋሪዎቿ በሙሉ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ልታደርግ መሆኗን አሳወቀች፡፡ከተማዋ የ11 ሚሊየን ህዝብ መኖሪያ ነች፡፡

~ ከ56 ቀናት እረፍት በኃላ በፈረንሳይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መከፈት ጀምረዋል፡፡በቀጣይ ሳምንት በሚሊየን የሚቆጠሩ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ያቀናሉ፡፡

~ የሊባኖስ የመንግስት ካቢኔ ከነገ ግንቦት 5 አንስቶ እስከ ሰኞ ድረስ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴ መገደቡን ይፋ አደረገ፡፡በሀገሪቱ 870 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸዉ ሲነገር የ26 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *