መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 7፣2012-ግዙፉ በፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማራዉ ማስተር ካርድ ሰራተኞች ከስራችን እንቀነሳለን ብለዉ እንዳይሰጉ ሲል አስታወቀ

በአሜሪካ ከኮሮና ቫይረስ ቀዉስ ጋር በተያያዘ ባለፉት ሁለት ወራት ከ30 ሚሊየን በላይ ዜጎች ስራቸዉን አጥተዋል፡፡በሀገሪቱ በፋይናንስ አገልግሎት የተሰማራዉ ማስተር ካርድ በክፍያ ስርዓት በመላዉ ዓለም ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘ ኩባንያ ነዉ፡፡

የማስተር ካርድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አጄ ባንጋ ሰራተኞች ስራዬን አጣለዉ ብለዉ እንዳይሰጉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ይልቅስ ለራሳቸዉ፣ለቤተሰቦቻቸዉ እና ለደንበኞች ጤና ሊያስቡ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ለማስተር ካርድ ከኮሮና ቀዉስ በፊት እንደነበረዉ ጊዜ ከዚህ ችግር በኃላ በቶሎ ለመመለስ ሊያዳግት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ማስተር ካርድ ከ54 ዓመታት በፊት በኒዉዮርክ ምስረታዉን ያደረገ ሲሆን በመላዉ ዓለም ከ20ሺ በላይ ሰዎችን ቀጥሮ ያሰራል፡፡በዓመት 12 በሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢን ኩባንያ ያገኛል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *