መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 7፤2012-በቤንሻንጉል ጉሙዝ አዋጁን የተላለፉ 1 ሺህ 209 ሰዎች ተቀጡ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብዙሃን ድርጅት ፤ ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉ 1 ሺህ 209 ግለሰቦች መቀጣታቸውን በክልሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረ ኃይል ገለጸ፡፡

ባለፈው እንድ ሳምንት አዋጁን የተላለፉ 683 የሚኒባስ፣ባጃጅ እና ሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች እያንዳንዳቸው ከ600 እስከ 3 ሺህ ብር
በሚደርስ ገንዘብ መቀጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ምክንያት የሌለው የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 391 ነጋዴዎች ድርጅታቸውን ከማሸግ ጀምሮ በገንዘብ መቀጣታቸውን አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም ቤንዚን በጥቁር ገበያ ሲሸጥ የተደረሰበት አንድ የነዳጅ ማደያ ባለቤት ጨምሮ አዋጁን የተላለፉ ሌሎች 180 ሰዎች ደግሞ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

58 መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎችም አዋጁን ተላልፈው በመገኘታቸው የታሸጉ ሲሆን ባለቤቶቹ ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን ገልፀዋል ።

ምንጭ፡-ኢዜአ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *