መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 7፤2012-በጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑካን ቡድን በጎንደር ዩንቨርስቲን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ህክምና ማዕከልን ጎበኘ።

በጉብኝቱም ከጤና ሚኒስትሯ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና
ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተና የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ተገኝተዋል።

ማዕከሉ ለኮሮናቫይረስ ህክምና የሚውል 320 አልጋዎችን ያዘጋጀ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ
24ቱ ለጽኑ ህሙማን የሚውሉ ናቸው።

ልዑኩም በተመሳሳይ በከተማው የተዘጋጁ የለይቶ ማቆያዎችንም ይጎበኛል።

በተጨማሪም በባህር ዳር ከተማ መሰል ጉብኝቶችን እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *