መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 7፤2012-በትምህርት ሚኒስቴር እና ስቴምፓወር በጋራ የተቋቋመ ዲጂታል የመፈብረኪያ ቤተ-ሙከራ በይፋ ስራ ጀመረ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር ከስቴም ፓዎር (STEMpower.org) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመ ሲሆን ከቅድመ-መደበኛ እስከ ቅድመ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ለህፃናት መጫወቻ፣ ለፈጠራ ስራ፣ ለማስተማሪያና ለአዲስ ግኝት መፍጠሪያ ተስማሚና ምቹ የሆነ የዕውቀትና ክህሎት ቅንጅት መፍጠሪያ ቦታ የ STEMpower /fablab/ ፋብላብ (ዲጂታል የመፈብረኪያ ቤተ-ሙከራ) ተቋቁሟል፡፡

ትምህርት ቤቶች ዝግ ከመሆናቸውና ተማሪዎች ቤት ውስጥ ከመዋላቸው ጋር በተያያዘ ጊዜያቸውን ለፈጠራ ተጠቅመው የሚያመጧቸውን ፈጠራዎች ወደ ምርትና አገልግሎት ማሻሻል በመስገባት የማህበረሰቡን ችግር በመፍታት አስተዋጻኦ እንደሚኖረውም ተገልጷል፡፡

ዛሬ በይፋ የተከፈተው ዲጂታል የመፈብረኪያ ቤተ-ሙከራ የቅድመ ኮሌጅ ተማሪዎችን ትኩረት በማድረግ በተለይ ከኮቪድ 19 ጋር የተያያዙ የፈጠራ ስራዎችን በጋራ በመደገፍ በተቋቋመው የማምረቻ ላቦራቶሪ ተጠቅመው የሚሰሩና ተግባር ላይ የሚውሉ ፕሮቶታይፖችን እስከሚያመርቱ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግ ስለመሆኑ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሣያል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *