መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 8፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በካምቦዲያ የ36 ዓመት እድሜ ያላት ሴት ከቫይረሱ ነጻ ሆና ከሆስፒታል መዉጣቷን ተከትሎ ክትትል የሚያደርግ ህሙማን በሆስፒታል የለም ተባለ፡፡በካምቦዲያ 122 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ ሁሉም ማገገመቸዉን እና ሞት አለመመዝገቡን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አስታዉቋል፡፡

~ በፈረንሳይና ጣልያን በድጋሚ የባህር ዳርቻ መዝናኛዎች ክፍት ተደረጉ፡፡ፖሊስ አላስፈላጊ የሆነ መሰብሰብን የማቋረጥ ስልጣን አለዉ፡፡ገቢዋ በቱሪዝም ላይ የተመሰረዉ ግሪክ አስቀድማ የባህር ዳርቻዎችን ክፍት አድርጋለች፡፡

~ ፓኪስታን የሀገር ዉስጥ በረራ ከከተማ ወደ ከተማ እንዲደረግ ፈቀደች፡፡የቫይረሱ ተጠቂዎች ከ38ሺ በላይ ሲደርስ የ834 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ወደ ኬንያ እና ሶማሊያ ጉዞ እንዳይደረግ ከለከሉ፡፡ክልከላዉ የወጪ ገቢ ንግድን ባይመለከትም ሹፌሮች አስገዳጅ የቫይረሱ ምርመራ ይደረግላቸዋል፡፡በኬንያ የቫይረሱ ተጠቂዎች 830 ሲደርስ የ50ቹ ህይወት አልፏል፡፡

~ በኒዉዮርክ የ14 ቀናት መመሪያን በመተላለፍ በባህር ዳርቻ ሲዝናና የነበረዉ ቱሪስት በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡የ23 ዓመት እድሜ ያለዉ ይህዉ ሰዉ በባህር ዳርቻ ሲዝናና የተነሳዉን ፎቶ በኢንስታግራም ገጹ ላይ በማጋራቱ ሊያዝ ችሏል፡፡

~ በሳዑዲ አረቢያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 51‚980 ሲደርስ የ302 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ በአማካይ በቀን ከ1‚500 በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተጠቁ ይገኛል፡፡

~ በደቡብ አፍሪካ የፕላቲንየም ማዕድን ማዉጫ ስፍራ 19 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉን ተከትሎ በጊዜዓዊነት ስፍራዉ ዝግ ተደረገ፡፡ደቡብ አፍሪካ ቁጥር አንድ የአለማችን ፕላቲንየም አቅራቢ ሀገር ናት፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *