መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 10፤2012-ለምን ከሌላ ሰው ጋር ትደንሻለች በሚል ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ የገደለው ግለሰብ በ 13 ዓመት እስራት ተቀጣ


የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ በ-#አዳማ ከተማ መስተዳድር #አባ_ገዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ #ጉርሙ ልዩ ቦታው እመቤት ጭፈራ ቤት ውስጥ ነው።
ተከሳሽ አብዲሳ ቱልቻ የተባለው ወጣት ከሟች ሳላስብሽ ጫላ ጋር በተጠቀሰው ጭፈራ ቤት ውስጥ አብረው በመዝናናት ላይ ሳሉ “እንዴት ከሌላ ሰው ጋር ትጨፍሪያለሽ” በማለት በጩቤ ሆዷ ላይ አንድ ጊዜ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ያደርጋል።
በስፍራው በተሰማው ጩኸት በአቅራቢያው የነበሩ የፖሊስ አባላት ከስፍራው ደርሰው ተከሳሽን በቁጥጥር ስር በማዋል ሟችን ለመረጃ ወደ አዳማ ሆስፒታል ይወስዷታል።
ፓሊስ የምርመራ መዝገቡን በማጣራት ለአዳማ ዞን አቃቤ ህግ ይልካል። አቃቤ ህጉም ክስ መስርቶ ለ-#አዳማ ልዩ ዞን ከ/ፍ/ቤት ያቀርባል።
ፍ/ቤቱም መዝገቡን መርምሮና አጣርቶ ተከሳሽም ድርጊቱን መፈፀሙን በማመኑ በ 13 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲሉ በአዳማ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነትና ከፍተኛ ባለሙያ ረ/ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *