መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 10፤2012-በሆንግ ኮንግ የሚገኙ የአሜሪካ ጋዜጠኞች ስራ ላይ ቻይና ጣልቃ እየገባች ነው ሲሉ ማይክ ፖምፒዮ ሀገሪቱን አስጠነቀቁ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ፀሀፊ ማይክ ፖምፒዮ በሆንግ ኮንግ በስራ ላይ የሚገኙ የአሜሪካ ጋዜጠኞች ስራቸውን እንዳይተገብሩ ፤ ቻይና የማስፈራራት ተግባር እየፈፀመች እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡
ቤጂንግ በራስ ገዝ አስተዳደሯ ሆንግ ኮንግ ላይ የምታሳድረው ጫና አሜሪካ በግዛቲቷ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በምታደርገው ግምገማ ላይ ጫና እያሳደረ ስለመሆኑ ገልፀው ፤ ከዚህ ድርጊቷ ትታቀብ ዘንድ አሳስበዋል፡፡
ዋና ፀሀፊው ፖምፒዮ “እነዚህ ጋዜጠኞች ነፃ የሚዲያ አባላት ናቸው ፣ የቻይና ህብረተሰብንና ዓለምን የሚጠቅም ዘገባን የሚጠቁሙ እንጂ የፕሮፓጋንዳ ማስፈፀሚያ አለመሆናቸው ሊታወቅ ይገባል” ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *