መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 10፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች


~ በእስራኤል በሪሞት የሚከፈትና የሚዘጋ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ተሰራ።ከ3 እስከ 10 የእስራኤል ሼክል ዋጋ የተቆረጠለት ሲሆን ለመመገብ እና ለመጠጣት መክፈት የሚያስችል ነው።
~ የአለም የጤና ድርጅት አመታዊ ጉባዔ በቨርቿል ስብሰባ በዛሬው እለት ሲጀመር አሜሪካ ተቃውሞ አሰማች።የአሜሪካ የጤና ዋና ፀሀፊ አሌክስ አዛር ድርጅቱ ግልፅነት ሊኖረው ይገባል የበርካቶች ህይወት በመረጃ እጥረት አልፏል ሲሉ ኮንነዋል።

~ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የመኪና አምራች ተቋማት በድጋሚ በከፊል ወደ ምርት እየገቡ ይገኛል፡፡ጀነራል ሞተር፣ፊያት እና ፎርድ ወደ ስራቸዉ ከተመለሱት መካከል ናቸዉ፡፡የተሸከርካሪዉ ኢንዱስትሪ የአሜሪካ 6 በመቶ የኢኮኖሚ ድርሻ አለዉ፡፡
~ የታንዛኒያ ዋንኛ የተቃዋሚ ፓርቲ ACT ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ የተጠቂዎችን ቁጥር እየደበቁ ነው ሲል ተቸ።
~ በሞሮኮ እንቅስቃሴ የሚከለክለው ህግ እስከ ሰኔ 10 ተራዘመ።7ሺ የሚጠጉ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲኖሩ 192 ሞት ተመዝግቧል።
~ ኳታር አየር መንገድ የበረራ ሰራተኞች እና መንገደኞች ማስክ እንዲጠቀሙ አስገዳጅ መመሪያ ይፋ አደረገ።

~ በፖላንድ ከሁለት ወራት በኃላ በድጋሚ የንግድ እንቅስቃሴ ተጀመረ።
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *