መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 10፤2012-የዓለም የጤና ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በዛሬው እለት ስብሰባ ያካሂዳሉ


ዓመታዊው የዓለም የጤና ድርጅት ምክር ቤት በአባል ሀገራቱ ልዑካን በጄኔቫ ይካሄድ የነበረ ሲሆን ፤ ይህንን በአካል ማድረግ ባለመቻሉ በኢንተርኔት (ቨርቹዋል) ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡ የዘንድሮ ጉባኤ ፖለቲካዊ ድባብ አጥልቶበታል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት በዛሬው ውይይት ታይዋን ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት በታዛቢነት መታደም እንድትችል ውይይት ይደረጋል፡፡
ታይዋን ቫይረሱን በመቆጣጠር ረገድ ትልቅ ስኬት ብትጎናፀፍም ፤ በዓለም የጤና ድርጅት በኩል ተገልያለሁ የሚል ቅሬታን አቅርባለች፡፡
15 የሚጠጉ ሀገራት ለታይዋን ተሳትፎ ለዓለም የጤና ድርጅት ደብዳቤ ፅፈዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *