መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 11፤2012-በቪዲዮ ጌም ጨዋታ ላይ እንደተመለከቱ ከህንጻ ላይ የዘለሉት ልጆቻቸዉ የተጎዱባቸዉ ወላጆች የቪዲዮ ጌም ኩባንያዉን እንከሳለን አሉ

በቻይና የ11 እና የ9 ዓመት እድሜ ያላቸዉ አንድ ወንድም እና እህት በኮሮና ቫይረስ ቀዉስ ከቤት ያለመዉጣት መከልከሉን ተከትሎ ሚኒ ወርልድና ፒስ በተባሉ የቪዲዮ ጌም ጨዋታዎች ይጠመዳሉ፡፡ልጆቹ ወላጆቻቸዉ በገዙላቸዉ ስማርት ስልክ በቀን ለስምንት ሰዓታት ያህል ሳያቋርጡ ይጫወታሉ፡፡

እነዚሁ ልጆች ታዲያ በቪዲዮ ጌም ላይ እንደተመለከቱት ከመኖሪያ ቤታቸዉ 15 ሜትር ከፍታ ላይ ለመዝለል ይወስኑና ያደርጉታል፡፡አይኖቻቸዉን ጨፍነዉ ከከፍታዉ ላይ ሲዘሉ በቪዲዮ ጌሙ ላይ እንደተመለከቱት በአየር ላይ እየተንሳፈፉ የሚመለሱ ቢመስላቸዉም ያ ሳይሆን ቀርቶ ለሆስፒታል ይዳረጋሉ፡፡የአጥንት ስብራት እና ቀዶ ጥገና ለጠየቀ ከፍተኛ ጉዳት አጋጥሟቸዋል፡፡

ልጆቹ የቪዲዮ ጌም ሱሰኛ እንዲሆኑ ምክንያት የሆነዉ የቪዲዮ ጌሙ አቅራቢ ተቋም የሆነዉ ቴንሴንት ነዉ ሲሉ ወላጆች ለመክሰስ ጉዞ ቢጀምሩም ቴንሴንት ኩባንያ ለዚህ ተጠየቂ መሆን የለብኝም ሲል አስታዉቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *