መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 11፤2012-አጫጭር መረጃዎች

~ በእየሩሳሌም የሚገኙ ሙስሊሞች ለሁለት ወር ከሚጠጋ ጊዜ በኃላ በአል አቅሳ መስጊድ በቀጣዩ ሳምንት ክፍት እንደሚደረግ በፍልስጤም የሚገኙ የሀይማኖት መሪዎች አስታወቁ፡፡

~ በፓኪስታናዊዉ እዉቅ የቴኒስ ተጫዋች ኳሪሽ አማካይት የተጀመረዉ ለፓኪስታን ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ ላይ የአለማችን ቁጥር አንድ የቴኒስ ተጫዋች ኖቫክ ጆኮቪች ተሳታፊ ሆነ፡፡በኮሮና ቀዉስ ድጋፍ ለሚያሻቸዉ የፓኪስታን ዜጎች የሚዉል ነዉ፡፡

~ በኳታር ማረሚያ ቤት ዉስጥ የኮሮና ቫይረስ በስፋት መዛመቱን ሂዉማን ራይትስ ዎች ቢያስታዉቅም የኳታር መንግስት ግን አስተባብሏል፡፡በኳታር ከ35ሺ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲኖሩ የ15 ሰዉ ሞት ሪፖርት ተደርጓል፡፡

~ ታንዛኒያ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ተጥሎ የነበረዉ የአየር በረራ መነሳቱን አሳወቀች፡፡የሀገሪቱ መንግስት በኮሮና ቫይረስ ዙርያ የላላ እርምጃ እየወሰደ ነዉ በሚል እየተተቸ ይገኛል፡፡

~ በእንግሊዝ የስራ አጦች ቁጥር በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ 69 በመቶ መጨመሩን የሀገሪቱ መንግስት ይፋ አደረገ፡፡

~ በፖርቹጋል በርካታ ሱቆችና ምግብ ቤቶች መከፈት ጀመሩ፡፡ባሳለፍነዉ የእረፍት ቀናት ጠቅላይ ሚንስትር አንቶኒዮ ኮስታ ግብይት ሲፈጽሙ በሊዝበን ከተማ በቴሌቪዥን የተላለፈ ሲሆን እንቅስቃሴ ዳግም መመለሱ ማመላከቻ ሆኗል፡፡

~ የአለም የጤና ድርጅት ባካሄደዉ ጉባዔ በኮሮና ቫይረስ መዛመት ዙሪያ ገለልተኛ በሆነ አካል እንዲጣራ ከስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ቫይረሱ በመላዉ ዓለም የ320,807 ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *