መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 12፤2012-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና የተሰጠው የትሪፖሊ መንግስት የጄነራል ሀፍታር ሀይሎች ስር የነበሩ ከተሞችን ማስለቀቁ ተሰማ


በካሊፍ ሀፍታር ጦር ስር የነበሩና በቱኒዝያ ድምበር አቅራቢያ የሚገኙት ባዳር እና ቲጄ የተባሉ ከተሞችን አስለቅቀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አል ዋቲያ የተባለ በደቡባዊ ትሪፖሊ የሚገኝን የአየር ሃይል የጦር ሰፈርን የትሪፖሊ መንግስት ተቆጣጥሯል፡፡
የሀፍታር ሀይሎች ቃል አቀባይ አህመድ አል ሚስማሪ ሽንፈት እንደደረሰባቸው አልሸሸጉም፡፡ ‹‹በድጋሚ የአየር ሃይሉ የጦር ሰፈር እንረከባለን›› ሲሉ ዝተዋል፡፡
ሊቢያ በትሪፖሊ መንግስት እና በጄነራል ካሊፍ ሀፍታር ሃይሎች እጅ ስር ከወደቀች ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *