መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 12፤2012-የካሜሮን ፕሬዝዳነት ኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ ከተዛመት ከሁለት ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዝምታቸዉን ሰብረዋል


ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ከሁለት ወራት ቆይታ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡በቫይረሱ ስርጭት የተነሳ ካሜሮን ከፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ነጻ የወጣችበት ብሄራዊ በዓል እንደማይከበር አስታዉቀዋል፡፡
የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የጤና ባለሙያዎች እያደረጉት ስለሚገኘዉ ርብርብ ፖል ቢያ አመስግነዋል፡፡ፖል ቢያ የኮሮና ቫይረስ በካሜሮን መዛመቱ ከተነገረ በኃላ ላለፉት ሁለት ወራት ከመገናኛ ብዙሃን እይታ መራቃቸዉ የጤና ችግር አጋጥሟቸዉ ሊሆን እንደሚችል በስፋት ሲነገር ቆይቷል፡፡
የ87 አመቱ አዛዉንት ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ላለፉት 38 ዓመታት በስልጣን ወንበር ላይ ይገኛሉ፡፡በካሜሮን 3,529 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲገኙ የ140 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *