መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 13፤2012-በአዲስ አበባ የተለያዩ ሃሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተለያዩ ሃሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ስሙ ዘውዴ ግሮሰሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተለያዩ ሃሰተኛ የሆኑ 26 ማህተሞች፣ ቲተሮች፣ በፍ/ቤት ክርክር ውሳኔ ያገኙ ሃሰተኛ ሰነዶች ፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ድረስ የተዘጋጁ የትምህርት ማስረጃዎች ይዟል፡፡
በተጨማሪም 1 ኮምፒተር 1 ኮፒ ማሽን 2 ሲፒዩ እንዲሁም የተለያዩ የልደት እና የጋብቻ ሰርቲፊኬቶች በስፍራው ማግኘቱን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ መርመሪ ዋና ሳጅን አብደልከድር መህዲ ተናግረዋል፡፡

በክፍለ ከተማው ከዚህ በፊትም የተለያዩ ሃሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡
ሃሰተኛ ሰነዶች በህዝብና በመንግስት አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ የሚያስከትለውን ከፍተኛ ጉዳት በመገንዘብ ወንጀለኞችን በመጠቆም የህብረተሰቡ ተባባሪነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *