መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 13፤2012-በአዳማ ከተማ ከ 195 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ህገ ወጥ የኮትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር ዋለ


በአዳማ ከተማ መስተዳድር ዳቤ ክፍለ ዳቤ ሹሉቄ ቀበሌ ልዩ ቦታው ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የዋጋ ግምቱ 195 ሺ 410 ብር የሚያወጣ ህገ ወጥ የኮትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
አቃዎቹ በዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ ከወለንጪቲ ወደ አዳማ ከተማ በመጓዝ ላይ እንዳለ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መያዛቸው ተገልጿል፡፡
የተያዙት እቃዎች አጠቃላይ ብዛታቸው 12 ሺ 803 ሲሆን እነዚህም ልባሽ ጨርቆች ፣ የተለያዩ ሲጃራዎችና ሺሻዎች ፣ መድሀኒቶች እንዲሁም የቴሌቪዥን ሪሞቶች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡
የተያዘው እቃ ለአዳማ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ገቢ መደረጉን እና አሽከርካሪዉ በቁጥጥር ስር ውሎ ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ በአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ መሰል ህገ ወጥ ድርጊቶች ሲፈፀሙ ለፓሊስ ጥቆማ በመስጠት በጋራ መከላከል ይኖርበታል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *