መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 13፤2012-በደቡብ አፍሪካ የሁለት ቀን እድሜ ያለዉ ጨቅላ ህጻን በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ


የኮሮና ቫይረስ ካለባት እናት የተወለደዉ ጨቅላ ህጻን በተወለደ በሁለተኛዉ ቀን በቫይረሱ ህይወቱ አልፏል፡፡የሀገሪቱ የጤና ሚንስትር ዚዊሊ ሚክሂዚ እንደተናገሩት ጨቅላዉ ህጻን እንደተወለደ የሳምባ ችግር እንዳጋጠመዉ መለየት የተቻለ ሲሆን በመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ እንዲተነፍስ ተደርጎ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡በቫይረሱ ህይወቱ ማለፉን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡
በአፍሪካ ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ያሉባት ሀገር ደቡብ አፍሪካ ስትሆን የቫይረሱ ተጠቂዎች 18‚003 ሲደርስ ከነዚህ መካክል 8‚950 ሰዎች አገግመዋል፡፡የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ እንደሚያሳየዉ በደቡብ አፍሪካ 339 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *