መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 13፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ የቦሊቪየ የጤና ሚንስትር በሙስና ቅሌት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ሚንስትሩ ማርሴሎ ናቫጃስ ከስፔን ኩባንያ የመተንፈሻ መሳሪያ በተጋነነ ዋጋ መግዛታቸዉ ምርመራ የተደረገ ሲሆን በፕሬዝዳንቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ተከትሎ ከስልጣን ተነስተዋል፡፡

~ በስፔን የኮሮና ቫይረስ ባስከተለዉ ቀዉስ ከስድስት ህጻናት በአንዱ ላይ ድብርት(ድባቴ) ማስከተሉን ሴቭ ዘ ችልድረን በሰራዉ ጥናት ተረጋገጠ፡፡ስፔን 28ሺ የሚጠጉ ዜጎቿን በቫይረሱ ተነጥቃለች፡፡

~ በሌጎስ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ፖሊስ ቃሉን አልጠበቀም በሚል የተጠራዉ አድማ እንዲያቆሙ ጥሪ ቀረበ፡፡የጸጥታ አካላት ህመምተኛ የጫነ አምቡላንስን ሳይቀር ያስቆማሉ በሚል የናይጄሪያ የህክምና ባለሙያዎች ማህበር አድማ መጥራቱ ይታወሳል፡፡

~ በጃፓን ቶኪዮ እና አካባቢዉ የተጣለዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቀጣዩ ሳምንት ሊያበቃ እንደሚችል ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ተናገሩ፡፡

~ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ95ሺ በላይ ሆነ፡፡በአፍሪካ 95‚201 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ 2‚997 ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡38‚075 ሰዎች ማገገማቸዉን የአፍሪካ ሲዲሲ ሪፖርት አድርጓል፡፡

~ በደቡባዊ የመን ኤደን የኮሮና ቫይረስ ህክምና ማዕከል ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ቢያንስ 68 ሰዎች ህይወታቸዉ ማለፉን ድንበር የለሹ የሀኪሞች ቡድን አስታወቀ፡፡በየመን ባለስልጣናት ከተገለጸዉ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች እንዳሉ ተነግሯል፡፡

~ በሜክሲኮ በሊግ ዉስጥ የሚጫወቱ ስምንት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ሪፖርት ተደረገ፡፡ክለቡ ሳንቶስ ላጉና የሚባል ሲሆን ተጫዋቾቹ የቫይረሱ ምልክት አልታየባቸዉም ነበር፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *