መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 13፤2012-የቶኪዮ ከፍተኛ አቃቢ ህግ የኮሮና ቫይረስ መመሪያን በመተላለፉ በቁማር ጨዋታ ላይ መጠመዱን ተከትሎ ከስራ

መልቀቁ ተሰማ በጃፓን ቶኪዮ ከፍተኛ አቃቢ ህግ ሂሮሙ ኩሮካዋ የሀገሪቱ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል መሰብሰብን ቢያግድም ይህንን ችላ በማለት በቁማር ፓርቲ ላይ ታድመዋል፡፡በዛሬዉ እለት ይፋዊ የስራ መልቀቂያ እንደሚያስገቡ ይጠበቃል፡፡
የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ሂሮሙ ኩሮካዋ የጃፓን ጠቅላይ አቃቢ ህግ አድርገዉ ለመሾም በዝግጅት ላይ እንደነበሩ ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡በጃፓን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ16ሺ በላይ ሲደርስ የ771 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *