መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 13፤2012-በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰው በመሰባሰብ ጫት ሲቅሙ የተገኙ 36 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው 20 ሺህ ብር እና በእስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎትም 21 ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ እና ሃያ ሺህ ብሩን መክፈል ያልቻሉ 15ቱ ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው በ15 ቀን እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *