መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 14፤2012-በግፍ ህይወቱን ያጣዉ የጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ወንድ ልጅ ለአባቱ ገዳዮቹ ምህረት ማድረጉን አስታወቀ

እ.ኤ.ኤ በ2018 በቱርክ የሳዑዲ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ህይወቱን የተነጠቀዉ የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ወንድ ልጅ ሳላህ ካሾግጂ ለአባቱ ገዳዮች ቤተሰቡ ይቅርታ ማድረጉን ይፋ አድርጓል፡፡ሳላህ በዚህ በተቀደሰ የረመዳን ወር የበደሉንን ይቅር ማለት አለብን ሽልማቱን ከፈጣሪ እናገኛለን ብሏል፡፡

ግድያዉን በተመለከተ አንዳንድ የምዕራባዉያኙ ሀገራት አልጋ ወራሹ ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን ከግድያዉ ጀርባ እጃቸዉ እንዳለበት በይፋ መናገራቸዉ ይወሳል፡፡ሳዑዲ አረቢያ በጀማል ካሾግጂ ግድያ እጃቸዉ አለበት ያለቻቸዉን አምስት ሰዎች የሞት ብይን ማስተላለፏ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *