መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 15፣2012- አሜሪካዊዉ የቅርጫት ኳስ አሰልጣኝና የቀድሞ ኮከብ ፓትሪክ ኤዊንግ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ይፋ ተደረገ

ፓትሪክ ኤዊንግ በቅርጫት ኳስ የዉድድር ዘመኑ ዉጤታማ ተጫዋች የነበረ ሲሆን ይህንኑ ስኬቱን በአሰልጣኝነቱም መድገም ችሏል፡፡በዛሬዉ እለት በቲዉተር ገጹ ይፋ እንዳደረገዉ በቫይረሱ መጠቃቱን ሁሉም ሰዉ ራሱንና በአካባቢዉ ያለዉን ሰዉ ከቫይረሱ እንዲጠብቅ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በቅርቡ ህክምናዬ ጨርሼ እወጣለሁ ሲል ጨምሮ መልዕክት አስተላልፏል፡፡በመላዉ አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ከ1.6 ሚሊየን በላይ ሲደርስ ከዚህ ዉስጥ 404ሺ ያህሉ አገግመዋል፡፡በቫይረሱ ህይወታቸዉን የተነጠቁ ሰዎች 97,996 ቁጥር መድረሱን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያሳያል፡፡

ሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *