መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 15፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ እዉቁ እንግሊዛዊ ደራሲ ማይክል ሮዛን ከ47 ቀናት በኃላ ከጽኑ ህሙማን ማገገሚያ መዉጣቱ ተሰማ፡፡

~ የክርስቲያኖች ቅዱስ ስፍራ በሚባለዉ በእየሩሳሌም ከሁለት ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በነገዉ እለት ክፍት ይደረጋል፡፡የግሪክ፣አርሜንያ፣የሶርያና የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ አማኞችን ጨምሮ የግብጽ ኮፕተክ የሮማን ካቶሊክ ክርስቲያኖች የሚያመልኩበት ስፍራ ነዉ፡፡ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት ቦታ ነዉ ተብሎ ይታመናል፡፡

~ በፍልስጤም ጋዛ ሰርጥ የመጀመሪያዉ ሞት ተመዘገበ፡፡ህይወታቸዉ ያለፈዉ የ77 ዓመት እድሜ ያላቸዉ ሴት አዛዉንት ከግብጽ ከተመለሱ በኃላ በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ሪፖርት ተደርጓል፡፡

~ የቻይና ዉሃን ከተማ በትላንትናዉ እለት ብቻ ለ1,470,950 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረጓ ተሰማ፡፡የኮሮና ቫይረስ መነሻ በሆነችዉ ዉሃን ከተማ 11 ሚሊየን ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን በሁለት ሳምንት ዉስጥ ለከተማዋ ነዋሪዎች በሙሉ ምርመራ የማድረግ እቅድ እንዳላት ቻይና አስቀድማ አሳዉቃ ነበር፡፡

~ የኢራን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ እንዳስታወቁት በነገዉ እለት ሀይማኖታዊ፣ታሪካዊና ባህላዊ ስፍራዎች ለህዝብ ክፍት ይደረጋሉ፡፡ ኢራን በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የ7‚359 ዜጎቿን ህይወት ተነጥቃለች፡፡

~ ህንድ ከ41 ዓመታት በኃላ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ኢኮኖሚዋ ክፉኛ መጎዳቱ ተሰማ፡፡በህንድ የቫይረሱ ተጠቂዎች ከ131ሺ ሲበልጥ 3‚865 ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

~ በግንቦት መጀመሪያ በጀርመን ፍራንክፈርት በአንድ የአምልኮ ስነስርዓት ላይ ከነበሩ ሰዎች ከ40 በላይ የሚሆኑት በኮሮና ቫይረስ ስለመያዛቸዉ ሪፖርት ተደረገ፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *