መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 16፤2012-ታሊባን የኢድ አልፈጥር በዓልን በማስመልከት ለሶስት ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ከአፍጋኒስታን መንግስት ጋር መድረሱን ይፋ አደረገ

ታሊባን ከዛሬ ጀምሮ የኢድ አልፈጥርን በዓል ምክንያት በማድረግ ለሶስት ቀናት እስከ ፊታችን ማክሰኞ ከአፍጋን ወታደሮች ጋር የተኩስ ልዉዉጥ እንደማይኖር አሳዉቋል፡፡የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት አሻራፍ ጋሃኒ ጥሪዉን በመልካም በመቀበል የሀገሪቱ ወታደሮች ይህንን እንዲያከብሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የሶስት ቀናቱ የተኩስ አቁም ስምምነት በአፍጋን ምድር መረጋጋት እንዲፈጠር ያግዛል፡፡ቀጣይነቱ ላይ ግን ዋስትና የሌለዉ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2018 የዒድ የተኩስ አቁም ስምምነት በዓሉ ካበቃ በኃላ መጣሱ አይዘነጋም፡፡የታሊባን ቃልአቀባይ ዛቡላህ ሙጃሂዲን የታሊባን ታጣቂዎች በጠላት ሀይል ላይ እንዳይተኩሱ ራሳቸዉን በመከላከል ላይ ብቻ ትኩረት ያድርጉ ብለዋል፡፡

ኔቶ መራሹ ጥምር ጦር አልቃይዳን ለመደምሰስ የጀመረዉ ዘመቻ ታሊባንን ከአፍጋኒስታን የስልጣን ወንበር ቢያባርርም በአፍጋን ግን ታሊባን ሊሸነፍ አልቻለም፡፡በአሜሪካ ታሪክ ረጅሙ ጦርነት በሚል ይታወቃል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *