መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 17፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በቻይና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን የሚያስገድዱ የምሽት ቤቶች ወደ ስራ ተመልሰዋል፡፡ደንበኞች ወደ እነዚህ ቤቶች ሲገቡ ሙቀት የመለካት፣ስማቸዉንና ስልካቸዉን የመስጠት ግዴታ አለባቸዉ፡፡

~ በጃፓን ለሚዘጋጀዉ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒት መገኘት ቅድሚያ የሚሰጠዉ ስለመሆኑ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ተናገሩ፡፡የጃፓን ከቫይረሱ ነጻ መሆን ዋስትና አይሆንም ቶኪዮ ኦሎምፒክ ከመላዉ ዓለም አትሌቶች ይመጣሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

~ ለሁለት ወራት የዘለቀዉ እንቅስቃሴን የሚገታዉ ህግ በፍልስጤም ዌስት ባንክ በነገዉ እለት እንደሚያበቃ ተነገረ፡፡በዌስት ባንክ 3 ሞት ሲመዘገብ ከ400 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

~ በሞሪሽየስ ከ28 ቀናት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሁለት ሰዎች ተገኙ፡፡ሞሪሽየስ ከኮሮና ጋር ያላትንጦርነት ማሸነፏ ከሁለት ሳምንት በፊት መናገሯ ይታወሳል፡፡

~ በግሪክ በድጋሚ ለሀገር ዉስጥ ቱሪስቶች የጉብኝት ስፍራዎች ክፍት ሲደረጉ፤ቼክ ሪፐብሊክ በተመሳሳይ የመዝናኛ ስፍራዎችን ክፍት አድርጋለች፡፡በዩክሬን መዲና ኬቭ የባቡር አገልግሎት በዛሬዉ አለት ተመልሷል፡፡በዩክሬን ቫይረሱ የ623 ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፡፡

~ በፈረንሳይ ለጤና ባለሙያዎች የሚሰጠዉ ክፍያ እንደሚጨምር የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስትር ኢዱዋርድ ፊሊፔ ቃል ገቡ፡፡

~ ሞንቴኔግሮ ከአዉሮጳ ቀዳሚዋ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ የሆነች ሀገር ናት ሲሉ ጠ/ሚ ዱስኮ ማርኮቪች ተናገሩ፡፡ከ69 ቀናት በፊት በሀገሪቱ የመጀመሪያ የቫይረሱ ተጠቂ ሲገኝ አጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 324 በመድረስ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ባለፉት 20 ቀናት በቫይረሱ የተያዘ ሰዉ በሞንቴኔግሮ አልተገኘም፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *