መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 18፤2012-በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ አንድ የፖሊስ አባል በጉልበቱ አንገቱ ላይ በመርገጥ የሰው ህይወት ሲያጠፋ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ይፋ ሆነ

ነጭ የፖሊስ አባል ድርጊቱን በአንድ ጥቁር አሜሪካዊ ላይ ሲፈፅም የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ገፅ ትስስር ላይ ከተጋራ በኃላ የሚኒያፖሊስ የፖሊስ ቢሮ ስለ መረጃው እውነታነት በማረጋገጥ ወደ ሆስፒታል ካቀና በኃላ ህይወቱ ማለፉን ይፋ አድርጓል።

ኤፍ.ቢ.አይ ስለጉዳዩ እያጣራ መሆኑን እና ሁለት የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር አውሏል።በ40ዎቹ የእድሜ ክልል ይሆና የተባለው ግለሰቡ መተንፈስ እንዳቃተው ከህልፈቱ በፊት ሲናገር ነበር። ከስድስት ደቂቃ በላይ በእንዲህ አይነት ሁኔታ መቆየቱ ተጠቁሟል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *