መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 18፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ድጋፍ ለሚስፈልጋቸዉ ሰዎች ያበረከቱት ምግብ የተበከለ ነዉ መባሉን አስተባበሉ፡፡ምግቡን የተመገቡ ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት አምርተዉ የከፋ የጤና ሁኔታ ላይ ናቸዉ ቢባልም ሩቶ የፖለቲካ ዝርፊያ ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

~ በኒዉዮርክ የሌሎችን ህይወት ለማትረፍ ሲሉ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቤተሰብ ልዩ ተጠቃሚ እናደርጋለን ሲሉ የኒዉዮርክ ገዢ አንድሪዉ ኩሞ ቃል ገቡ፡፡ የጤና፣የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎችና የድንገተኛ ሰራተኞች በዋናነት ይገኙበታል፡፡

~ የብሩንዲ የጤና ሚንስትር በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል በሚል የሚናፈሰዉ መረጃ የሀሰት ነዉ ሲል የሀገሪቱ መንግስት አስተባበለ፡፡ ሚንስትሩ ኒዲኩማን ለግል የጤና ጉዳይ ወደ ኬንያ ያቀኑ ሲሆን ሀሙስ እለት ወደ ብሩንዲ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

~ የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስከፊዉን የስርጭት ደረጃ በማለፋችን ለሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት የድል መታሰቢያ በዓል ዝግጅት ይደረግ ሲሉ ለመከላከያ ሚንስትር ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ናዚ ጀርመን ላይ የተገኘዉ የ75ኛ ዓመት ድል በዓል በሰኔ መጨረሻ ይከበራል፡፡በራሺያ የቫይረሱ ተጠቂዎች 376ሺ ደርሷል፡፡

~ በአለም ዙርያ ለኮሮና ቫይረስ ክትባትና መድሃኒት በሚል 10.4 በሊየን የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ቃል መገባቱን የአዉሮጳ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

~ ቼክ ሪፐብሊክ በዛሬዉ እለት ከኦስትሪያና ጀርመን ጋር የሚያዋስናት ድንበር ከፈተች፡፡ከስሎቫኪያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር በነገዉ እለት ይከፈታል፡፡

~ በቺሊ በ24 ሰዓት ዉስጥ 5ሺ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ሲነገር ሁለት የመንግስት ሚንስትሮች እንዳሉበት ተረጋግጧል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *