መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 20፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ በቲውተር ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ከቻይና የተሰጠ እጅግ በጣም መጥፎ ስጦታ ሲሉ ገልፀውታል።

~ በማላዊ 400 የሚጠጉ ሰዎች ከለይቶ ማቆያ ውስጥ ማምለጣቸው ተሰማ።ለአያያዝ ምቹ አይደለም በሚል ቅሬታ ግለሰቦቹ ከለይቶ ማቆያ ስፍራ አምልጠዋል።በሀገሪቱ 101 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ የ4 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል።

~ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የአለም የቱሪዝም እንቅስቃሴ 70 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።ይህ አይነቱ የቱሪዝም መቀዛቀዝ ከ1950ዎቹ ወዲህ የመጀመሪያው ነው።

~ በአውሮጳ የፀረ ወባ መድሃኒት ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን መስጠት ቢታገድም ኢንዶኔዥያ ግን መድሃኒቱን ከመስጠት እንደማታቆም አስታወቀች።ሁለት የፀረ ወባ መድሃኒቶችን ኢንዶኔዥያ ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን መስጠቷን ቀጥላለች።

~ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ መግባቱ ተሰማ።አየር መንገዱ ለሰራተኞቹ የግንቦት ወር ደሞዝ የሚከፍለው እንደሌለው አስታውቋል።

~ በወርሃ ሚያዚያ ብቻ 850ሺ ፈረንሳውያን ከስራ ገበታቸው መፈናቀላቸው ተሰማ።በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሣ 4.5 ሚሊየን ፈረንሳውያን ስራ አጥ ሆነዋል።

~ በእንግሊዝ ከ15 ሰው አንዱ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅቶ እንደነበር በአንቲቦዲ አማካኝነት በተደረግ ምርመራ ሲረጋገጥ 7 በመቶ እንግሊዛውያን በቫይረሱ ተይዘው እንደነበር ሪፖርት ተደርጓል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *