መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 21፣2012-በአሶሳ ከተማ 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሀሽሽ ወይም ካናቢስ ዕጽ በቁጥጥር ስር ዋለ

በአሶሳ ከተማ ወረዳ ሁለት ቀጠና 2 ልዩ ስሙ ኤፍታ ሆቴል አካባቢ በተደረገ ክትትል 6 ኪ.ግ የሚመዝን ሀሽሽ ወይም ካናቢስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አስታውቋል።

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዋና የስራ ሂደት ም/ኢ/ር ደረጀ ኢታና እንደገለጹት ከክትትል ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት በተደረገው ቁጥጥር አቶ አበበ ተሾመ የተባለ ግለሰብ 6 ኪሎ ግራም ሀሽሽ ይዞ ለመሸጥ ሲስማማ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ግለሰቡ ከዚህ በፊት በከተማችን ከሀሽሽ ሱስ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ግድያ ወንጀል በጊዜዉ አከፋፋይ እንደነበረ ታዉቆ ሲፈለግ የነበረ እና ራሱን ደብቆ የተለያየ ስም እየተጠቀመ የቆየ መሆኑን እና የራሳቸዉ የተደራጀ ቡድን ያላቸዉ መሆኑን ገልፀዋል።

ፖሊስም ወንጀል ፈፃሚውን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደበት መሆኑን ም/ኢንስፔክተር ደረጀ ኢታና አክለዉ ገልጸዋል፡፡

ሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *