መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 22፣2012-በኢትዮጵያ ተጨማሪ 95 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 5034 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1063 መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
ተጨማሪ 11 ሰው ያገገመ ሲሆን እስካሁን 208 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው ሰዎች ከ 15 እስከ 80 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 71 ወንድና 24 ሴት ሲሆኑ 94 ኢትዮጵያውያንና 1 የህንድ ዜጋ ናቸው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-

~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ5034 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 94 ኢትዮጲያዉያን እና 1 ህንዳዊ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡

~ 71 ዱ ወንዶች ሲሆኑ 24 ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።እድሜያቸዉ ከ15 እስከ 80 ዓመት የሆኑ ናቸዉ።

~ የመኖሪያ ስፍራቸዉ 56 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣22 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣1 ሰዉ ከአፋር ክልል፣5 ሰዎች ከአማራ ክልል፣3 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣3 ሰዎች ከሀረር ክልል፣2 ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል

~ 30 ሰዎች የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡

~ 4 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት አላቸዉ፡፡

~ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ 61 ሰዎች ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 106,615 ደርሷል።

~ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 11 ሰዎች አገግመዋል።(2 ከትግራይ፣9 ከአፈር ክልሎች)

~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 208 ደርሰዋል።

~ በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ የሚገኝ አምስት ታማሚዎች አሉ ፡፡(በአንድ ጨምሯል)

~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 845 ናቸው።

~ የስምንት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *