መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 24፤2012-ኢራን ለአሜሪካ ባስተላለፈችው መልዕክት መንግስት ህዝቡን ሊሰማ ይገባል ብላለች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊተር ገፁ ባስተላለፈው መልዕክት አሜሪካ እንደጨካኝ ውሻ እና ለጦር ፍቅር ያላቸው የትራምፕ አስተዳደር ህዝቡን ሊሰማ ይገባል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የተስፋፋውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከሉ ላይ ትኩረት ማድረጉን ትቶ ፤ አስተዳደሩ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን ለማስፈራራት ተጨማሪ ወታደሮችን መቅጠርና እና አነፍናፊ ውሾችን መጨመሩን ተያይዞታል ብለዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ህዝቧን መስማትና የወደቀ መመሪያዋን ማስተካከል ይኖርባታል ሲሉ ምክራቸውን አክለዋል፡፡

አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ 1,837,170 ዜጎቿ የተጠቁ ሲሆን 106,195 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው ስለማለፉ ሪፖርት አድርጋለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *