መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 25፣2012-በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወጣው መግለጫ እንደደረሳቸው እና በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አበቤ አስታወቁ።

ወይዘሮ አዳነች በማህበራዊ ገፃቸው “ሰበዓዊ መብት የምናከብረው እና የምናስከብረው ለማንም ብለን ሳይሆን ለህዝባችን እና ለፍትህ ስንል ነው” ብለዋል።

በተቋሙ የወጣውን መግለጫ የማጣራት ስራው ተጠናቆ ምላሽ ለመስጠት በሂደት ላይ
እያለ፤መግለጫው በተለያዩ ሚዲያ መሰራጨቱንም ነው ዋና አቃቤ ህግ ያስታወቀው።

“አሁንም ቢሆን ዘገባዉን ከይዘቱ ፣ ከአካሄዱ ፣ እንዲሁም የጉዳዩን እውነተኛነት እና
ገለልተኛነት የማጣራት ስራችንን በቶሎ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው። በማጣራት ስራችን በሚገኘውም ውጤት ፣ ሪፖርቱ እውነት በሆነበት ልክ ፣ መወሰድ ያለበቸውን እርምጃዎች እንወስዳለን” ብለዋል ወይዘሮ አዳነች አቤቤ።

ሀሰት በሆነበት ወይም በተጋነነበት አኳያ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋራ በመወያየት ሪፖርቱ እንዲስተካከል ጥረት እንደሚደረግ ወይዘሮ አዳነች ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *