መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 25፣2012-በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 14 ደረሰ

የሟቾች ሁኔታ፦

~ 1ኛ የ30 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ህይወታቸው ያለፈ

~ 2ኛ የ56 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ በተጓዳኝ ህመም ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው ህይወታቸው አልፏል።ሁሉት ግለሰቦች ህይወታቸው ያለፈና ለአስክሬን ምርመራ ወደ ሆስፒታል በመጡበት ጊዜያት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

በኢትዮጲያ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 87 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1344 ደርሷል፡፡

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-

~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ 3932 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 87 ኢትዮጲያዉያን ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡

~59 ዱ ወንዶች ሲሆኑ 28 ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።እድሜያቸዉ ከ10 እስከ 70 ዓመት የሆኑ ናቸዉ።

~ የመኖሪያ ስፍራቸዉ 67 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 6 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣7 ሰው ከአማራ ክልል1 ሰው ከሀረሪ ክልል

~ 28 ሰዎች የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡

~ 18 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት አላቸዉ፡፡

~ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ 41 ሰዎች ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 116,309 ደርሷል።

~ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 14 ሰዎች አገግመዋል።( 6 ከኦሮሚያ እና 8 ከሶማሌ ክልሎች)

~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 231 ደርሰዋል።

~ በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ የሚገኝ ስምንት ታማሚዎች አሉ ፡፡(+4 ጨምሯል)

~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 1097 ናቸው።

~ የ 14 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *